Community event
No More ኖ more አስቂኝ ድራማ በቶሮንቶ
About this event
የአዘጋጁ መልእክት
ሰላም🙏
አዲሱ ዓመት እንዴት ጀመረ? ዛሬ አንድ መልዕክት ይዤ ነው የመጣሁት።
ለየት ያለ የጥበብ ማዕድ በአጋር አቅራቢነት በመደገስ ላይ ነኝ። ድግሱ “No More” የተሰኘ ኮሜዲ ነው። “No More” ታዋቂዋ ደራሲና ተዋናይት ሜሮን ጌትነት ከሚኒሶታ፣ ተወዳጇ ተዋናይት ሀና ዮሐንስ ከካልግሪ፣ የኮሜዲዋ ንግስት ትግስት ንጋቱ (ቲጂ) ከዲሲ፣ የዚህ ትያትር ክሪየቲቭ ፕሮዲውሰርና ምርጥ ተዋናይት ፍሬሕይወት መለሰ ከቶሮንቶ በአንድ መድረክ የሚገናኙበት ኮሜዲ ነው። በኢትዮጵያ የትያትር ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴቶች ብቻ የሚተውኑበት የመጀመሪያው ኮሜዲ መሆኑ ደግሞ ለየት ያደርገዋል።
እሑድ ኖቬምበር 1 በArmenian Youth Centre at 50 Hallcrown Pl, ከረፋዱ 3 ላይ በራችን ይከፈታል። በምርጥ የመድረክ ትወና አብረን የምንዝናናበት ዝግጅት እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ። ትኬት ($40) በኢትራንስፈር ወይም በካሽ ከወዲሁ የመግዣ መንገድ አመቻችተናል። ቀድመን ካልጨረስን ደግሞ በር ላይ $50 መግዛት ይቻላል።
ከአክብሮት ጋር፣
ጴጥሮስ
